Skip to main content

VisionFund MFI

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ከቪዥን ኮሚኒቲ ሆልሰቲክ ጋር በመሆን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደ።

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ከቪዥን ኮሚኒቲ ሆልሰቲክጋር በመተባበር “አረንጓዴ ለአካባቢያችን፤ አካታች ፋይናንስ ለህዝባችን” በሚል መሪ ሀሳብ የችግኝ ተከላመርሃ ግብር አካሄደ። በመርሃ-ግብሩ ላይ የተቋሞቹ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች፣ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በዕለቱም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 (ፈረንሳይ ግሬት አቢሲኒያ አካባቢ)እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 (ገነተ ፍሬ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ) ችግኞች ተተክለዋል። የተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች እንደገለጹት፣የተተከሉት ችግኞች ለቀጣዩ ትውልድ ንጹህ አየር፣ ጤናማ አካባቢ እና ዘላቂ ልማት የሚያስገኙ ሕያው አሻራዎች ናቸው ብለዋል። ተቋሙ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ጎን ለጎን፣ መሰል ማህበራዊና አከባቢያዊ ኃላፊነቶችን በንቃት መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ታህሳስ 13፥2018 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የፊርማ ስነ ሥርዓት ላይ እንደተገለፀው በስምምነቱ መሰረት ተቋሙ ቀልጣፋና ዘመናዊ የሆነ የውክልና፣የመመስረቻና ተያያዥ ሰነዶችን በአጭር ጊዜና በዲጂታል መንገድ ለማረጋገጥ የሚያስችለው ይሆናል። በተጨማሪም የስጋት አስተዳደር ስርዓትን በመዘርጋት የደንበኞችን የዋስትና ሰነዶች ደህንነት በመጠበቅና የሰነዶችን ህጋዊነት በማረጋገጥ የተቋሙን አሰራር ውጤታማነት እንደሚያጎለብት ተገልጿል። በመጨረሻም ስምምነቱ ደንበኞቻችን ሰነዶችን ለማረጋገጥ የሚወስድባቸውን አላስፈላጊ ጊዜና ወጪ በእጅጉ በመቀነስ የደንበኞችን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑ ተመልክቷል።

VisionFund Microfinance Enters $30 Million Strategic Partnership Agreement

ADDIS ABABA September 6, 2025– VisionFund Microfinance has signed a $30 million loan agreement with the International Finance Corporation (IFC), marking a major milestone in Ethiopia’s financial sector. This agreement represents IFC’s first-ever local currency loan (in Ethiopian Birr) to a financial institution in the country. VisionFund Microfinance has signed a $30 million loan agreement with the International Finance Corporation (IFC), with an initial disbursement of $10 million. The loan is intended to expand credit access for micro, small, and medium-sized enterprises (MSMEs) in Ethiopia, with at least half specifically allocated to businesses that are women-owned, women-led, or where women make up the majority of employees. In addition to financing, IFC’s targeted advisory services will strengthen our strategic business planning, risk management, and responsible finance practices as we advance to the next stage of our development. Ato Taye Chimdessa, the CEO of VisionFund Microfinance, stated that the partnership will reinforce the institution’s dedication to inclusive finance. He further noted that it will significantly improve VisionFund’s capacity to deliver effective financial services to clients and the wider community, thereby enabling them to achieve their objectives. Ethiopis Tafara, IFC Vice President for Africa, said the investment shows IFC’s strong commitment to supporting inclusive economic growth in Ethiopia. He noted that the partnership with VisionFund Microfinance will create lasting benefits for small businesses, especially those led by women, while also strengthening the country’s financial sector.

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ አዳዲስ ቅርንጫፎችን መርቆ ከፈተ።

ተቋሙ በደማቅ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት የቱሉዲምቱ እና ሳሪስ ቅርንጫፎችን በይፋ ስራ አስጀምሯል። በመክፈቻው ሥነ–ሥርዓት ወቅት የዋናው ቢሮ ተወካዮች፥ የማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሃላፊዎች፣ የአከባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች እና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል። አዳዲሶቹ ቅርንጫፎች ለማህበረሰቡ በቅርበት ተደራሽ በመሆን ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት በማቅረብ በኩል የሚኖራቸው ፋይዳ ጉልህ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዕለቱ የተገኙ ታዳሚዎችም አማራጭ የፋይናንስ አቅርቦት የሚሰጡ ቅርንጫፎች በአካባቢያቸው መከፈታቸው እንዳስደሰታቸውና በቀጣይም አብረው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል። በመጨረሻም ተቋሙ በቀጣይም ተደራሽነቱን በማስፋት ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑ ተመልክቷል።

አመታዊ አጠቃላይ የማኔጅመንት ጉባኤ ተካሄደ፡፡

የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አመታዊ የማኔጅመንት ጉባኤ ሀምሌ 10 እና 11 2017 ዓ.ም. በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በጉባዔው ላይ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታዬ ጭምዴሳን ጨምሮ የዋናው ቢሮ የተለያዩ የስራ ክፍል ሃላፊዎች፤ የአካባቢ ስራ አስኪያጆች እንዲሁም የ116ቱም ቅርንጫፎች ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል፡፡ በዕለቱ የ2024/25 (እ.ኤ.አ) የበጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለጉባዔው ከቀረበ በኋላ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የዕርስ በዕርስ የልምድ ልውውጥ በማድረግ ውጤታማ ተሞክሮዎችን ለመተግበር የሚያስችል የፓናል ዉይይትም ተደርጓል። በተጨማሪም ተቋሙ በቀጣይ አመት ለመተግበር ያቀዳቸውን አዳዲስ አቅጣጫዎች የሚያመላክቱ ገለጻዎች ቀርበዋል፡፡ ከውይይት በኋላ የማጠቃለያ ሃሳብ ያስተላለፉት አቶ ታዬ ጭምዴሳ ሁሉም ተሳታፊ አካላት የቁጠባ መጠን ማሳደግን፤ የተቋሙን ወጪ እና የሚበላሹ ብድሮችን መጠን መቀነስን እንዲሁም የላቀ የደንበኞች አገልግሎ ት አሰጣጥን በተመለከተ ልዩ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞች የዕውቅና መስጠት መርሃግብር የተከናወነ ሲሆን ሽልማቱን የሰጡት የተቋሙ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ እሌኒ መርጊያ ባስተላለፉት መልዕክት ከመደበኛው ስብሰባ ባሻገር፣ ይህ መድረክ የእርስ በእርስ ትስስር እንዲፈጠር እና ወዳጅነት እንዲጠናከር በማድረግ በኩል ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ሰው ተቋሙ የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ በባለቤትነት ስሜት በመስራት ከዚህ በእጅጉ የሚልቅ ውጤት ለማስመዝገብ ተግተው እንዲሰሩ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡