Locate our branches

Contact Us
Contact Us

ቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ የአዲስ ዓመት የንግድ አውደ-ርዕይ ላይ ተሳተፈ፡፡

ከነሃሴ 17/2015 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 6/2015 ዓ.ም ድረስ በኤግዚቢሽን ማዕከል በተካሄደው አውደ-ርዕይ ላይ 11 ቅርንጫፎች ተሳትፈዋል፡፡ 

ከአንድ ሺህ አራት መቶ በላይ አዲስ የቁጠባ ሂሳብ የተከፈተ ሲሆን ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል፡፡ እንዲሁም ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ቃል የገቡ ደንበኞችን ማግኝት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ተቋሙ የሚሰጣቸውን ነባርና አዳዲስ የቁጠባና የብድር አገልግሎቶችን በማስተዋወቅ በኩል ጥሩ ተሞክሮ የተወሰደበት አውደ-ርዕይ ነበር፡፡

የአዲስ ዓመት የዋዜማ መርሃ-ግብር በዋናው ቢሮ ተካሄደ፡፡

ጳጉሜን 6/2015 ዓ.ም የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታዬ ጭምዴሳን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ ሃላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ደማቅ መርሃግብር ተካሂዷል፡፡ የዕለቱ መርሃ-ግብር በጸሎት የተጀመረ ሲሆን የተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች መንፈሳዊ ትምህርትን ጨምሮ በተከታታይነት ቀርበዋል፡፡ 

በተጨማሪም በ2015 ዓ.ም የነበሩ ስኬቶችን መነሻ በማድረግ ለቀጣይ ዓመት ተግቶ በመስራት እቅዶቻችንን ሁሉ ማሳካት እንደሚገባ አቶ ታዬ ጭምዴሳ አስገንዝበዋል፡፡ በመጨረሻም የምሳ ግብዣ መርሃ ግብር የተደረገ ሲሆን የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክቶችንም በማስተላለፍ አዲሱ ዓመት የሰላም የጤና እንዲሁም የስኬት እንዲሆን በመመኘት የዕለቱን መርሃ-ግብር የመዝጊያ ጸሎት በማድረግ ተጠናቋል፡፡

የዋናው ቢሮ ሰራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ፡፡

መስከረም 5/2016 ዓ.ም የተቋማችን የማህበራዊ ሃላፊነት አካል የሆነው የደም ልገሳ መርሃግብር የተከናወነ ሲሆን ሰራተኞች በፈቃደኝነት ደም በመለገስ ለወገን ደራሽ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡ በዕለቱ የተገኙ ተሳታፊዎች እንደገለጹት የዚህ ዓይነቱ መርሃ-ግብር በተቋሙ የተለመደ ሲሆን ውድ የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት የመታደግን ዕድል ስለሚሰጥ ደም በመለገስ መርሃ-ግብር መሳተፋቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡