Locate our branches

Contact Us
Contact Us

የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የትግበራ እቅድውይይት ተካሄደ፡፡

የ2015 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የትግበራ ዕቅድ ዉይይት በኔክሰስ ሆቴል ነሐሴ 2 እና 3 ፣ 2015 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በእለቱ የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ታዬ ጭምዴሳን ጨምሮ ምክትል ሥራ አስፈጻሚዎች ፤የዋናው ቢሮ የተለያዩ የስራ ክፍል ሃላፊዎች፤ የአካባቢ ስራ አስኪያጆች እንዲሁም ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡ 

በወቅቱ በ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞች ፤ መሻሻል የሚገባቸው ተግባራት እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡በተጨማሪም የዚህ ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የየአካባቢው የማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች የትግበራ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ 

በወቅቱ በ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞች ፤ መሻሻል የሚገባቸው ተግባራት እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡በተጨማሪም የዚህ ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የየአካባቢው የማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች የትግበራ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በመቀጠልም የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአካባቢ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች የዕውቅና መስጠት መርሃግብር ተከናውኗል፡፡በዚህም መሰረት የማዕከላዊ ምስራቅ አካባቢ አንደኛ ደረጃ የወጣ ሲሆን የምዕራብ አካባቢ እና የማዕከላዊ ሰሜን አካባቢ በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን አግኝተዋል፡፡

በመጨረሻም የዋናው ቢሮ ሰራተኞች እና የአካባቢ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ሥራአስኪያጆች የቪዥንፈንድ ማይክሮፋይናንስ ተቋም በዚህ አመት ላደረገው ልዩ የደመወዝ ጭማሬ የምስጋና ስጦታ አበርክተዋል፡፡ ሽልማቱን የተቀበሉት አቶ ታዬ ጭምዴሳ ባስተላለፉት መልእክት ሁለም ሠራተኞች በባለቤትነት ስሜት ሆነው ለ2016 ዓ.ም በሁለም ዘርፍ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸው በተለይም ከፍተኛ የአመለካከት ለውጥ በማምጣት የቁጠባ ገንዘብ መጠናችንን በእጅጉ ለማሻሻል ተግተው እንዲሰሩ ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡